ጥር  ፳፯ ቀን ፪፲፻፬ ዓመተ ምሕረት።

ከዚህ ቀደም መስከረም ፲፪ ቀን ፪፲፻፬ ዓመተ ምሕረት በተጻፈ ደብዳቤ፡ የኛ የኢትዮጵያውያን እጅግ የበዛው ክፉ ሥራችን፡ ከፈጣሪ አምላካችን ደርሶ፡ እግዚአብሔርን አስቆጥቷልና፡ በኢትዮጵያ ላይ ከሰማይ የቅጣት እሳት እንደሚወርድ፣ እሳቱ ሁሉንም እንደሚጎበኝ፡ የቀረበውን ማስታወሻና ማስጠንቀቂያ ይስታውሷል።

እኔ የዚህ ደብዳቤ ጸሐፊ አሁን የምኖረው በአሜሪካ አገር ነው። በኢትዮጵያ በአካል ተገኝቼ ይህ እንደዚህ ሆነ እያልኩ ዜና ላቀርብ አልችልም። በዜና የሚቀርበውን ደግሞ ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጋር አብሬ አያለሁ፣ አነብባለሁም። ዓለማዊ የዜና አውታሮች ከሃሰት ጋር የተቆራኙ የቅጥፈት አራማጆች በመሆናቸው ስለ እውነተኛው፣ ስለመንፈሳዊው ነገር መመስከር አልፈለጉም። የሚፈልጉበት ጊዜ ይመጣል። ያን ጊዜ ቢፈልጉት ያገኙታልን?  ካገኙትስ ዜና ለማቅረብ አቅም ይኖራቸዋልን? ጥር ፳፭ ቀን ፪፲፻፬ ዓመተ ምሕረት አንድአድርገን የተባለ መንፈሳዊ የመልእክት ሰሌዳ ጎበኘሁ፣ ከዚህ በታች የሚታየውን መልእክት አነበብኩ።  በመልእክት ሰሌዳው ላይ የሚታዩትን ፎቶግራፎችና መልእክቶችን ወስጄ የማሳሰቢያ መልእክት ለማስተላለፍ እጠቀምባቸው ዘንድ የመልእክት ሰሌዳውን አዘጋጅ በጽሁፍ ልጠይቅ ሞከርኩ። መልእክት አዘጋጂውን በተዘዋዋሪ መንገድ ጥያቄየ እንዲደርሳቸው ብሞክርም ላገኛቸው አልቻልኩም። ይሁንና የዜና ምንጩን ጠቅሼ  ለኢትዮጵያውያን ስለሁኔታው ብነግር አዘጋጂውን አልበድልምና ያነበብኩትን ክስተት ዝርዝርና ያየኋቸውን ፎቶግራፎች ክዚህ መልእክት በታች አስፍሬያለሁ።

ማሳሰቢያ'፥

አንድአድርገን ተብሎ በሚጠራው ሰሌዳ የቀረበውን ዜና በማየት በሆሳዕና አቅራቢያ የሚታየው ማስጠንቀቂያ ይሁነን። በእሳት ከመበላታችንና የኢትዮጵያ ምድር በእቶነ እሳት ጋይቶ በነዳጅ እንደተመረዘ መሬት እንዳይሆንብን ሁላችንም ፈጥነን ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፣ ምህረቱንም ከቸርነቱ እንሻት። ይህ ቁጣ የመጣው የተዋህዶ ክርስቲያኖች ባልሆኑ ላይ ብቻ አይደለም። ስህተት በፈጸሙ የተዋህዶ የክርስትና አማኞችም ላይ ብቻ አይደለም። ክፉ በሠሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ሁሉ ይመጣል። ለክፉ የወረደ ጻድቃንንም ሊዳስስ ይችላል። በተለይ ጻድቃን ክፉን ነገር አይተው በቸልታ አልፈውት ከሆነ።    

ምን እናድርግ?

ካህናቶችን ለእግዚአብሔር እንተዋቸው። እግዚአብሔር ከነሱ ጋር የሚያደርገውን ንግግር ማን ያውቃል? ስለእኛ ስለራሳችን ስለ መሃይምናን ኢትዮጵያውያን እንነጋገር። 

እኛ ኢትዮጵያውያን የሌብነት ወንጀል ፈጽመናል፣ የእግዚአብሔርን ሰርቀናል። ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር ፈቃድ፣  በሕዝብ የደስታ ሆይታ፣ በመንግሥት አዋጅ፣ በእምቢልታ፣ በቤተክህነት ምስክርነትና ቡራኬ፡ ለእግዚአብሔር የተሰጠች አገር ናት። ለእግዚአብሔር የተሰጠን አሥራት የሚነጥቅ፣ መልሶስ የሚወስድ  ማን ነው? ነጣቂውስ የእግዚአብሔርን ወስዶ ሳይታወክ ሊኖር ይቻለዋልን? የኢትዮጵያ ንጉሧ እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለም። የእግዚአብሔር እንጂ የሰውም አይደለችም። በኢትዮጵያ ሊኖር የሚችል ዙፋን የመድኃኒአለም ነው። ከእግዚአብሔር ዙፋን አጠገብ የሌላ አምልኮ ወንበር ሊሰለፍ ከቶ አይችልም። እነሆ እኛ ከንቱዎች የእግዚአብሔርን ዙፋን ለቅርጫ አቅርበን አርክሰናል። የእግዚአብሔርን ክብር ለሌላ ስለሰጠን ለየብቻችን መታወክ፣ በህብረት መታወክ፣ በውስጥ መታወክ፣ በውጭም መታወክ እንጂ ደስታ፣ ሰላምና ልምላሜ መቼ አለን? መቼስ ሳንታወክ ኖረን እናውቃለን? ማን ያውቃል ከዚህ ከሚመጣው የመአት እሳት ተቀጭነት ይልቅ ሌላ የይቅርታ መላን ሊሠራልን ይችላልና፥ ከጾምና ከጸሎት ጋር የሚከተለውን እናድርግ፥

፩ኛ -  ከሁሉም በፊት  እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ "ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር አገር ናት፣ ባለቤቷም፣ ንጉሧም እግዚአብሔር ነው።" እያለ ያለፍርሃት፣ ያለ ይሉኝታ፡ በአንደበቱ ይናገር። በዘመዶቹ፣ በወገኖቹ፣ በኢትዮጵያ ጠላቶችም ፊት ቢሆን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይህንኑ ከአሁኑ ሰአት ጀምሮ መመስከር አለበት።  እያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት ሴትም እንዲሁ መመስከር አለባት።

፪ኛ -  ህግ ማለት የእግዚአብሔር ህግ እንጂ  በእግዚአብሔር  ያልተባረከ የተውሶ የሰው ህግ ወይም  የሰው ፍልስፍና ወይም የሰው ርእዮተ አለም   በኢትዮጵያ እንዳልተፈቀደ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ማመን አለበት። ማንኛውም የውጭ አገር ፍልስፍና፣ አምልኮም ሆነ አፍራሽ ትምህርት በኢትዮጵያ ሊሰለጥን አልተፈቀደም። እንዲህ አይነቱ ነገር በኢትዮጵያ ጥፋትን ያስከትላልና። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሰውን ፍልስፍና አስወግዶ በእግዚአብሔር ህግ ለመጓዝ፣  ለእግዚአብሔርም ህግ ለመታዘዝ በልቡ ለእግዚአብሔር ቃል መግባት አለበት። ይህን በማህበር መግለጥም መልካም ነው።  

፫ኛ -  ሁሉም ኢትዮጵያዊ በያለበት ይነጋገር። ይሰባሰብ፣ ይመካከር። ምክሩም ለአንድ ጉዳይ ብቻ ነው። እሱም፥ ከዛሬ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሃምሳ አመት ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በጋራ በእግዚአብሔር ላይ የፈጸሙት እያንዳንዱ ክፉ ሥራ ተዘርዝሮ ይመዘገብና ኢትዮጵያውያን በሙሉ፥ አረጋዊ፣ ብርቱ፣ ደካማ፣ ጤነኛ፣ በሽተኛ፣ እናት፣ አባት፣ ልጅ፣ ወጣት፣ ኮረዳ፣ ህጻንም ሳይቀር  ኢትዮጵያውያን በሙሉ በኢትዮጵያ ተሰብስበው በለቅሶና በጸጸት እግዚአብሔርን ይቅርታ የሚጠይቁበት የአንድ የጋራ ጊዜ ቀነ ቀጠሮ ለመያዝ ነው።  የይቅርታ መጠየቂያው የጸጸት ቀን ከአንድ ቀን እስከ አንድ ሳምንት ሊሆን ይችላል። የይቅርታ መጠየቂያ ቦታዎቹም የተ የት እንደሚሆኑ ዝግጅቱ ካለ ይወሰናል።  

ጆሮ ያለው ይስማ፣ አይን ያለው ይመልከት፣ ህሊና ያለው ያስተውል፤ በኋላ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት እንዳይሆን።

ክብር ለመድኃኒአለም ይሁን።

ሙሉጌታ።
ጥር  ፳፯ ቀን ፪፲፻፬ ዓመተ ምሕረት።

ሁለተኛ ማሳሰቢያ። ለኢትዮጵያውያን በሙሉ።

 HOME
የመረጃ ምንጭ፥   http://andadirgen.blogspot.com/2012/01/blog-post_31.html

ሆሳህና ላይ ከሰማይ የወረደው እሳት ያደረሰው አደጋ


(አንድ አድርገን ጥር 22 2004. ) ከሆሳዕና ከተማ ከሁለት እከከ ሶስት ሰዓት የእግር መንገድ በሚወስድ ቦታ ላይ ባለው የበናራ መድሀኒዓለም ዙሪያ ቁጥሩ ከአርባ የማያንስ ቤት ተቃጥሏል  እሳቱ ከምሰሶ መሃል ይያያዛል ፤ሲያሰኘው ከመሰረት ይጀምራል ሲለው ከጣራ ጀምሮ ያቃጥላልሰሞኑን የቆጮ ጉድጓድ ሳይቀር ተቃጥሏል…. የሚገርመው አንድም የኦርቶዶክስ አማኝ ቤት አልተቃጠለም…አሳቱ ላቃጠላቸው ሰዎች የተዘረጋ ድንካንም ተቃጥላል….የመጀመሪያዎቸሁ ቤት ተቃጥሎባቸው ቤት ካሰሩ ሰዎች መሃከል ድጋሚ ሁለቱ ቤታቸው ተቃጥላል…. የሚገርመው ቤት ሲቃጠል አንዱ ቤት ብቻ ይቃጠላል እንጂ እሳት ለጎረቤት ቤቶች አያልፍም ፤ምንም አንኳን ቤቶቹ ተነካክተው ቢሰሩም

በተጨማሪ ደግሞ ቤቱ ሲቃጠል እልል ከተባለ እሳቱ እቃ እስኪወጣ ጊዜ ይሰጣል ነገር ግን ከተጮሀ ጊዜ አይሰጥም ….ማውደም ነው፡፡ ሲያወድም ደግሞ ቀሪ ነገር እንኳን አይተርፍም ምሰሶ እንኳን አመድ ይሆናል….ቤቶቹ ደግሞ በጣም ተራርቀው በወንዝ ተለያተው የሚገኙ ናቸው….ሁሉም ቤቶች የሚቃጠሉት በቀን ነውእንድም ቤት በማታ አልተቓጠለም….በነገራችን ላይ የደብሩ ዲያቆን እንደነገረኝ ከሶስት ዓመት በፊት ምንጩ ያልተወቀ አሳት በመቅደስ ውስጥ ተነስቶ የመንበሩን ጉልላት ብቻ በልቶ ሌላ ሳይነካ ጠፍታል እናም የአሳቱ መነሻ / ውስጥ ነው እየተባለ ነው……
ሆሣዕና ተዓምር የበዛባት ከተማ ሆናለች ከተወሰነ ዓመት በፊት ስዕል በዛፍ ላይማር ከዛፍ ላይ…. ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ….. አሁን ደግሞ የቤት ቃጠሎ….


ከቤተክርስትያናችን ላይ እጃቸውን አስካላወረዱ ድረስ እግዚአብሔር በዚህ መልኩ ሲቀጣቸው ይኖራል ፤ እኛ ቤተክርስትያን ላይ የሚደርሰው ነገር ግድ ባይሰጠን እንኳን እግዚአብሔር ግን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ሰውን ከጥፋቱ እዲመለስ ያስተምራል ፤ ከወራት በፊት ቤተክርስትያናችንን አቃጥለውብናል ፤ ክርስያኖችን በሰይፍ አሳቀዋል ፤ መንግስት የመደባቸው ፖሊሶች ሳይቀሩ መከላከል እና ማርገብ ሲገባቸው ፤ ቀጥተኛ ተሳታፊ ሆነው ጉዳት ሲያደርሱ ተመልክተናል ፤ እኛ ግን አምላካችን አይተወንም ፤ አይረሳንም ፤ ከእኛ የሚጠበቀው ፀንቶ ፈተናን ተቋቁሞ በክርስትና መኖር ብቻ ነው ፡፡  በቤተክርስትያን ላይ እጃቸውን አንስተው ያቃጠሉ ሰዎች አይናችን እያየ የሳምንት እድሜን መዝለቅ አልቻሉም ፤ በኤሌክትሪክ አደጋ ህይወታቸውን ሲነጠቁ ተመልክተናል ፤ መንግስት ጉዳታችን እያየ  ፍትህ ላለመስጠት ወደ ኋላ ቢልም ፤እኛ ግን ወደ ኋላ የማይል በስራቸው መጠን ልክ የሚበቀል አምላክ አለን ፤ እግዚአብሔር ይመስገን ፤ አሁን የእኛ ምኞት ከደረሰባቸው ቁጣ ይድኑ ዘንድ እግዚአብሔር በምህረት አይኑ ይመለከታቸው ዘንድ የደረሰባቸውን ነገር ተመልክተው ልብ ቡገዙ ምኞታችን ነው

በፎቶ ያደረሰውን ነገር ይመልከቱ

ኮባ ስር የወረደው እሳት

የተሰበሰበ እህል ላይ

ቤታቸውን ያሳጣቸው ሰዎች

የአካባቢው ሰዎች ተሰብስበው በጉዳዩ ሲወያዩ