"ደወል፡ ሰንጠረዥ፡" በሚል፡ አርእስት፡ ሪቻርድ፡ ኸርንስታይን፡ እና፡ ቻርልስ፡ ሙሬይ፡፡የተባሉ፡ የሃርቫርድ፡ ዩኒቨርስቲ፡ እና፡ የአሜሪካን፡ ኢንተርፕራይዝ፡ ድርጅት፡ "ስመጥር፡ ምሁሮች፡" በጋራ፡ በጻፉት፡ መጽሐፋቸው፡ "ጥቁሮች፡ ብሩህ፡ አእምሮ፡ የላቸውም፣ የማሰብ፡ ችሎታቸው፡ ከነጮች እጅግ፡ ያነሰ፡ ነው፡" በማለት፡ ብዙ፡ በአኃዝ፡ የተደገፉ፡ መረጃዎችን፡ አሰፈሩ። ብዙ፡ የአሜሪካ፡ ምሁራኖችም፡ ከፍ፡ ከፍ፡ በሉ፡ አሏቸው። ስለ፡ ጉዳዩም፡ በየጉባኤው፡ ፊት፡ እየቀረቡ፡ በተለይ፡ በህይወት፡ የቀሩት፡ አንደኛው፡ ጸሐፊ፡ ምስክርነት፡ ሰጡ። በመጽሐፋቸው፡ ያቀረቡት፡ የመደምደሚያ፡ ሃሳብና፡ የመጽሐፉም፡ ዋናው፡ አላማ፡ ጥቁሮች፡ አእምሮ፡ የጎደላቸው፡ መኾኑ፡ ከተፈጥሮ፡ እንጂ፡ ጭቆና፡ ስለደረሰባቸው፡ አይደለምና፡ ለነሱ፡ የሚደረግ፡ የበጎ፡ አድራጎት፡ እርዳታ፡ ለውጥ፡ አያመጣምና፡ መቆም፡ አለበት፡ የሚል፡ ነው። ለአሜሪካ፡ ይበጃል፡ ብለው፡ እነዚህ፡ ሁለት፡ ምሁሮች፡ "የጥቁር፡ ዘር፡ ይጠፋ፡ ዘንድ፡ ጥቁሮች፡ ልጅ፡ እንዳይወልዱና፡ እየጠፉ፡ እንዲሄዱ፡ የሚያግዝ፡ የመንግሥት፡ ፖሊሲ፡ ያስፈልጋል፡" የሚል፡ የመፍትሔ፡ ሃሳብ፡ በመጽሐፋቸው፡ መደምደሚያ፡ ላይ፡ አቅርበዋል። ይህን፡ ሃሳባቸውን፡ ብዙ፡ የአሜሪካን፡ ምሁራን፡ ወደውላቸዋል። 

 ሪቻርድ፡ ኸርንስታይን፡ እና፡ ቻርለስ፡ ሙሬይ፡ የጥቁር፡ ዘር፡ ወደፊት፡ በህይወት፡ እንዳይኖር፡ የተማጠኑበት፡ ምክንያት፡ በቀጥታና፡ በተዘዋዋሪ፡ በመጽሐፉ፡ ተገልጿል። ለዚህ፡ መጽሐፋቸውም፡ ድርሰት፡ መነሳሻ፡ የኾነው፡ አንዱና፡ የተደበቀው፡ አላማ፡ በምድር፡ ላይ፡ የሚገኝ፡ የተፈጥሮ፡ ፍሬ፡ እያነሰ፤ የሰው፡ ቁጥር፡ ደግሞ፡ እየጨመረ፡ በመምጣቱ፡ አንዳንድ፡ ህብረተሰቦች፡ በደስታ፡ እንዲኖሩ፡ ሌሎች፡ ህብረተሰቦች፡ በህይወት፡ መኖር፡ የለባቸውም፡ ብሎ፡ የተነሳው፡ የኢዩጀኒክ፡ ተልእኮ፡ ነው።  በቀጥታ፡ የተገለጸው፡ አንዱ፡ ምክንያት፡ ጥቁሮች፡ ከአእምሮ፡ ብሩህነት፡ እጥረት፡ የተነሳ፡ ልጅ፡ ማሳደግና፡ ቤተሰብን፡ ደግፈው፡ መያዝ፡ ስለማይችሉ፡ ጤናማውን፡ ህብረተሰብ፡ ይበክላሉ፡ የሚል፡ ነው። ይህን፡ ያሉበት፡ ሌላው፡ በተዘዋዋሪ፡ የተገለጸው፡ ምክንያት፡ ደግሞ፡ "ጥቁሮች፡ ጠለቅ፡ ብለው፡ ማሰብ፡ አይችሉምና፡ ከውጭም፤ ከውስጥም፡ ለሚሰነዘር፡ ጥቃት፡ ደካማ፡ ጎን፡ በመኾን፡ አሜሪካን፡ ያስጠቃሉ፡" የሚል፡ ፍራቻ፡ ነው።     

ለመሆኑ፡ እነዚህ፡ ሰዎች፡ ይህን፡ ደካማ፡ አእምሮ፡ ያስጠቃል፡ የሚለውን፡ ተመክሮ፡ ከየት፡ አገኙት? መልሱም፡ ከአጥቂነትና፡ እንደ፡ ኢትዮጵያ፡ ካሉ፡ ተጠቂ፡ አገሮች፡ ልምድ፡ በመውሰድ፡ ነው።

አንድ፡ እንቁ፡ የያዘ፡ ሰው፡ እንቁውን፡ በብጣሽ፡ መዳብ፡ የሚቀይረው፡ ባለመዳቡ፡ መዳቡ፡ ከእንቁው፡ ይበልጣል፡ ብሎ፡ ሲያሳምነው፡ ነው። መዳብ፡ ከእንቁ፡ ይበልጣል፡ ብሎ፡ ያመነ፡ ባለእንቁ፡ አንድም፡ ህፃን፡ ነው፤ ህፃን፡ ካልሆነ፡ ደግሞ፡ እነ፡ ቻርልስ፡ ሙሬይ፡ የአሜሪካን፡ ወርቅ፡ በመዳብ፡ እንዳይቀይር፡ ሰግተው፡ በህይወት፡ እንዳይኖር፡ እንዳሉት፡ ያለ፡ ዝቅተኛ፡ የማሰብ፡ ችሎታ፡ ያለው፡ ሰው፡ ነው። ምእራባውያን፡ ብዙ፡ ኢትዮጵያውያን፡ እንቋቸውን፡ በመዳብ፡ ሲቀይሩ፡ አይተዋልና፡ ትምህርት፡ ወስደውበታል።

እንቁ፡ ያስጣሉ፡ መዳቦች።

ኢትዮጵያ፡ ከንጉሥ፡ ዳዊት፡ አብራክ፡ በወጡ፡ ነገሥታት፡ አስተዳደር፡ ስትኖር፡ በተለይ፡ በመጨረሻዎቹ፡ አንድ፡ መቶ፡ አመታት፡ የንጉሥ፡ ሹማምንት፡ በሆኑ፡ ባለስልጣኖች፡ ጭቆና፣ ንጥቂያ፣ ግፍና፣ ጭካኔ፡ ይፈጸም፡ ጀመረ። ጌታና፡ ሎሌ፣ ባላባትነትና፣ ጭሰኝነት፣ ተገልጋይነትና፡ አገልጋይነት፣ ጨቋኝነትና፡ ተጨቋኝነት፡ እየበዛ፡ መጣ። ለረጂም፡ ጊዜ፡ የኢትዮጵያን፡ ባህሮች፡ ተራሮች፣ ሜዳዎቿን፣ ወንዞቿንና፣ ማእድኖቿን፡ ለመቆጣጠር፡  ይመኙና፡ ይሞክሩ፡ የነበሩ፡ የባእድ፡ አገር ሰዎች፡ ሙከራቸው፡ አልሳካ፡ ያለው፡ ኢትዮጵያውያን፡ ለአንድ፡ ንጉሥ፡ የሚታዘዙ፡ በታዛዢነታቸውም፡ ምክንያት፡ አንድ፡ ኾነው፡ የሚመክቱ፡ በመኾናቸው፡ ነው፡ ብለው፡ አጤኑ። የሚሹትን፡ ለማግኜት፡ መጀመሪያ፡ የኢትዮጵያውያንን፡ አንድነት፡ መበተን፡ እንደሚኖርባቸው፡ ተገነዘቡ። ይህን፡ የኢትዮጵያውያን፡ አንድነት፡ ለመበተን፡ ኢትዮጵያውያን፡ የንጉሥ፡ ሥርአትን፡ እንዲጠሉ፡ ማድረግ፡ እንዳለባቸውም፡ አወቁ። ኢትዮጵያውያን፡ ንጉሣቸውን፡ እንዲከተሉ፡ የሚያደርጋቸው፡ ዋነኛው፡ ምክንያት፡ ኃይማኖታቸው፡ እንደኾነም፡ በጥናታቸው፡ ደረሱበት። እነሆ፡ አሁን፡ በንጉሣዊ፡ አስተዳደር፡ ግፍ፡ መብዛቱ፡ በኢትዮጵያ፡ ላይ፡ አይናቸውን፡ ለጣሉ፡ ባእዳን፡ ውጥን፡ መግቢያ፣ መንደርደሪያ፡ መንገድ፡ ኾነ። 

የውጭ፡ አገር፡ ሰዎች፡ በከንቱ፡ ውዳሴና፡ በድለላ፡ ነገሥታቶቹን፡ በመቅረብ፡ "ሰዎቻችሁን፡ ዘመናዊ፡ ትምህርት፡ እናስተምርላችሁ፣ የስልጣኔ፡ ጮራ፡ እናብራላችሁ፡" ብለው፡ የሽንገላ፡ ወዳጅነትን፡ ፈጠሩ። ነገሥታቶቹም፡ ለብልጦቹ፡ የባእድ፡ አገር፡ ሰዎች፡ ልባቸውንና፡ በራቸውን፡ ከፈቱ። ጮሌዎቹም፡ በተከፈተው፡ በር፡ ገቡ። አከናወኑም። የአስኳላ፡ ትምህርት፡ ተጀመረ፤ ኢትዮጵያ፡ ለዘመናት፡ ያደለበችው፡ ፈሪሃ፡ እግዚአብሔር፡ ያለው፡ የትምህርት፡ ሥርአት፡ በአንድ፡ ምሽት፡ የእድሜ፡ ልክ፡ እስራት፡ ተፈረደበት። አረጀ፣ አፈጀም፡ ተባለ። ግዕዝ፤ ተዋረደ፤ ቦቦታውም፡ እንግሊዝኛና፤ ፈረንሳይኛ፡ ተከበሩ። ጥቂት፡ ቆይቶም፡ እግዚአብሔር፡ ተናቀ፤ በቦታውም፤ ቻርልስ፡ ዳርዊን፣ አልቨርት፡ አነስታይንና፡ ካርል፡ ማርክስ፡ ተመለኩ። ኢትዮጵያዊ፡ መምሰል፡ ረከሰ፤ የውጭ፡ አገር፡ ሰው፡ መምሰል፡ ከበረ። የጥንቶቹ፡ እስራኤላውያን፡ መና፡ እጅ፡ እጅ፡ አለን፡ ብለው፡ ግብጽን፡ እንደሻቱት፤   ምእራባውያን፡ በነደፉት፡ የትምህርት፡ ስርአት፡ ሰልጥነው፡ የምእራባውያን፡ ጮሌነት፡ የማረካቸው፡ ኢትዮጵያውያንም፡ የኢትዮጵያን፡ ታሪክ፡ እጅ፡ እጅ፡ የሚል፡ አፈታሪክ፡ የሚል፡ ስም፡ አወጡለት፡ ጣሉትም። በቦታውም፡ የምእራባውያንን፡ የጀብዱና፡ የስልጣኔ፡ ታሪክ፡ ልክ፡ እንደራሳቸው፡ ታሪክ፡ በመቁጠር፡ በጉጉት፡ ይጨልጡ፡ ጀመር። ጮሌዎቹ፡ የውጭ፡ አገር፡ ሰዎች፡ አሁንም፡ ዓላማቸውን፡ አልሳቱም። ኢትዮጵያን፡ እንደ፡ ብረት፡ አጥር፡ ሆኖ፡ ከባርነት፡ ከልሏት፡ በኖረው፡ በኃይማኖቷ፡ ላይ፡ ኢላማቸውን፡ አነጣጠሩ። ኃይማኖቷን፡ ጥላሸት፡ ለመቀባት፡ በኃይማኖቷ፡ ጉድፍ፡ የሚመስል፡ ነገር፡ የሚፈልጉ፣ ጉድፍ፡ የሚመስል፡ ባያገኙ፡ ደግሞ፡ መልካሙን፡ ነገር፡ ጉድፍ፡ የሚያስመስሉ፡ ጆሮ፡ ጠቢዎችን፡ "ስኮላሮች"፡ እያሉ አሰማሩ። ለነዚህ፡ "ስኮላሮቻቸውም"፡ ብዙ፡ ገንዘብ፡ እየሰጡ፡ ከተቀደሱት፡ ቦታዎች፡ የተቀደሱ፡ ታቦታትን፡ ከቤተክርስቲያናት፡ እያሰረቁ፡ አወጡ። የሰረቋቸውንም፡ ታቦታትና፡ የከበሩ፡ መጻህፍት፡ ለዚሁ፡ ኃይማኖቷን፡ ጥላሸት፡ ለመቀባት፡ አላማቸው፡ ተጠቀሙበት። ኃይማኖቷን፡ የሚያጣጥሉና፡ የሚያንቋሽሹ፡  በጥናት፡ የተዘጋጁ፡ ስንኞችን፡ የያዙ፡ ትምህርቶችን፡ በኢትዮጵያውያን፡ አእምሮ፡ የሚያሰርፁ፡ ጆሮ፡ ጠቢዎች፡ ፓስተር፡ የሚል፡ ማእረግ፡ እየተሰጣቸው፡ በኢትዮጵያውያን፡ አንድነት፡ ውስጥ፡ ሠረጉ። እነሱም፡ አእምሮ፡ የጎደላቸውን፡ ብላቴናዎች፡ በየማእዘኑ፡ በማባበል፡ አጠመዱ። በጥናት፡ የተዘጋጁትን፡ ስንኞችም፡ በአእምሯቸው፡ ውስጥ፡ አሠረፁባቸው። እነሱም፡ በተራቸው፡ ሌሎች፡ ብላቴናዎችን፡ እንዲያጠምዱ፡ አዘጋጇቸው። አዲሱ፡ ትምህርት፡ የሰረፀባቸው፡ እነዚህ፡ ብላቴናዎች፡  እንደታዘዙት፡ አከናወኑ። ኢትዮጵያውያን፡ ኃይማኖታቸውን፡ ናቁ። ኃይማኖታቸውን፡ ሲንቁም፡ ለንጉሥ፡ የሚገዙበት፡ ምክንያት፡ ተነነ። ለጠላት፡ እንደ፡ አንድ፡ የነበሩ፡ ጠላትነት፡ የእርስ-በርስ፡ ንብረታቸው፡ ኾነ።  

ኢትዮጵያውያን፡ በአንድ፡ ወይም፡ በሌላ፡ ንጉሥ፡ አስተዳደር፡ ጭቆና፡ ደረሰብን  ብለው፡ የኢትዮጵያን፡ የንጉሥ፡ አስተዳደር፡ ሥርአት፡ ከሥር፡ መሠረቱ፡ መገርሰሳቸው፡ ዓሳ፡ እሾኽ፡ አለው፡ ብሎ፡ ዓሳ፡ መብላት፡ እንደመተው፣ ወይም፡ ክፉ፡ ህልም፡ አዘወተርኩ፡ ብሎ፡ መተኛት፡ እንደማቆም፡ ያለ፡ እርምጃ፡ ነበር። ለምን?

የኢትዮጵያ፡ የንጉሥ፡ አስተዳደር፡ ሥርአት፡ የተቋጨው፡ በእግዚአብሔር፡ ቃልኪዳን፡ እንጂ፡ በሰው፡ ፈቃድ፡ አልነበረም። እግዚአብሔር፡ የእስራኤል፡ የንጉሣዊ፡ አስተዳደር፡ ከዳዊት፡ ዘር፡ እንዳይወጣ፡ ቃል፡ ገባ። በመንፈሳዊ፡ ቃልኪዳንነቱ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ከዳዊት፡ ዘር፡ ተወለደ። በህዝባዊ፡ የንጉሣዊ፡ አስተዳደር፡ የዳዊት፡ ልጆች፡ በኢትዮጵያ፡ (በአዲስ፡ ኪዳን፡ እስራኤል፡) በንጉሥነት፡ የክርስቶስን፡ ክብር፤ ጠባቂዎች፡ ሆነው፡ በሺህ፡ ለሚቆጠሩ፡ አመታት፡ ኢትዮጵያን፡ መሩ። ከነዚህ፡ ንጉሦች፡ አንዳንዶቹ፡ መልካሞች፤ አንዳንዶቹ፡ ደግሞ፡ ክፉዎች፡ ነበሩ። በእግዚአብሔር፣ ቃልኪዳን፡ የንጉሥነትን፡ ቦታ፡ ሲይዙ፡ ፍርድን፡ ሊያስተካክሉ፣ ህዝብን፡ ሊያሰማሩ፡ እንጂ፡ ሊበድሉና፡ ሊጨቁኑ፡ አልነበረም። ከእግዚአብሔር፡ መንገድ፡ ሲወጡ፡ ህዝብ፡ ወደ፡ እግዚአብሔር፡ መንገድ፡ እንዲመለሱ፡ መገፋፋት፡ ካልሆነ፡ ግን፡ ስልጣናቸውን፡ የእግዚአብሔርን፡ መንገድ፡ ለሚከተል፡ ሌላ፡ የዳዊት፡ ልጅ፡ እንዲለቁ፡ ማስጨነቅ፡ መልካም፡ ነበር። ኢትዮጵያውያን፡ በዚህ፡ መንገድ፡ ነበር፡፡አፄ፡ ሱስኒዮስ፡ ከኃይማኖት፡ መስመር፡ ሲወጡ፡ በልጃቸው፡ በአፄ፡ ፋሲል፡ እንዲተኩ፡ ያስገደዷቸው። አንድ፡ ንጉሥ፡ ስለበደለ፡ የንጉሥ፡ አስተዳደርን፡ ሥርአት፡ ገርስሶ፡ መጣል፡ በተለይ፡ ለኢትዮጵያ፡ በረከትን፡ የሚያስቀር፡ አምራሪ፡ እርምጃ፡ ነበር።  አንድ፡ ህብረተሰብ፡ ሞኝ፡ ካልሆነ፡ በቀር፡ እግዚአብሔር፡ የደነገገውን፡ ሥርአት፡ በሰው፡ ውጥን፡ አይተካም። እግዚአብሔር፡ የዳዊትን፡ ዘር፡ በኢትዮጵያ፡ አስቀርቶ፡ መቀባታቸው፡ ለኢትዮጵያ፡ መኾኑ፡ ለኢትዮጵያውያን፡ እጅግ፡ በጣም፡ እፁብ፡ድንቅ፡ የሆነ፡ በረከት፡ ነው። ይህን፡ ምእራባውያን፡ ወይም፡ እስያውያን፡ ወይም፡ አረባውያን፡ አላገኙትም። የምእራባውያንን፡ የማናናቂያ፡ አስተምህሮ፡ ተከትለው፡ የዳዊት፡ ዘር፡ በኢትዮጵያ፡ መቀባቱ፡ ሲወርድ፡ ሲዋረድ፡ ከመጣው፡ አፈ፡ ታሪክ፡ ውጭ፡ የተጻፈው፡ በክብረ፡ ነገሥት፡ ብቻ፡ ነውና፡ እንናቀው፡ ለሚሉ፡ የተቀባው፡ መስመር፡ በኢትዮጵያ፡ እንደሚውል፡ ዳዊት፡ እራሱ፡ በትንቢቱ፣ በእውን፡ መዋሉን፡ ደግሞ፡  ልጁ፡ ንጉሥ፡ ሰሎሞን፡ በጽሁፍ፡ አስፍሮታል። አሰፋፈሩም፡ የኢትዮጵያ፡ ጸጋ፡ ለኢትዮጵያ፡ ሳይሆን፡ ለሌላ፡ አገር፡ ነው፡ ለሚባል፡ የማደናገሪያ፡ ወሬም፡ ፋታ፡ አይሰጥም።

ከሁሉም፡ በላይ፡ ደግሞ፡ እግዚአብሔር፡ የወጠነውን፡ አንሻም፤ እኛ፡ እራሳችን፡ ከምእራባውያን፡ ፍልስፍና፡ ተውሰን፡ ምእራባውያን፡ በነጎዱበት፡ ጎዳና፡ እንነጉዳለን፡ ብለው፡ በትውስት፡ የፍልስፍና፡ ጎዳና፡ ሲጓዙ፡ ኢትዮጵያውያን፡ ምን፡ እንዳገኛቸው፡ እራሳቸው፡ ያውቃሉና፡ ያ፡ ያዋጣል፡ ካሉ፡ ምርጫው፡ የነሱ፡ ነው። ይህ፡ የኢትዮጵያውያን፡ ምርጫ፡ ከሆነ፡ ያስቡበት፡ ዘንድ፡ ይህ፡ መንገድ፡ ከአሥር፡ አመት፡ ባልበለጠ፡ ጊዜ፡ ውስጥ፡ ኢትዮጵያውያንን፡ የቅኝ፡ ተገዢ፣ አድርጓቸው፡ ብዙም፡ ሳይቆይ፡ በህይወት፡ መቆየት፡ እንኳን፡ የማይችሉበት፡ ዘመን፡ ሊጠብቃቸው፡ እንደሚችል፡ ሆነው፡ ይዘጋጁ። ከላይ፡ "ደወል፡ ሰንጠረዥ፡" ተብሎ፡ በተጠቀሰው፡ መጽሐፍ፡ የሰፈረውን፡ ምልክት፡ ለኔ፡ ብለው፡ ያስቡ። 

ዘመን፡ እያለቀ፡ ነው። ምግብ፡ ወይም፡ አቅርቦት፡ ሲያጥር፡ እንደ፡ ድሮው፡ ጉልበት፡ ያላቸው፡ አገሮች፡ ጉልበት፡ የሌላቸውን፡ ሄደው፡ በቅኝ፡ ገዢነት፡ ተቆጣጥረው፡ ጎን፡ ለጎን፡ የሚኖርበት፡ ዘመን፡ አልፏል። የተፈጥሮ፡ አቅርቦት፡ ስላነሰ፡ የቅኝ፡ ግዛት፡ ቀንበር፡ የሚወድቅባቸው፡ ሰዎች፡ በህይወት፡ ካሉ፡ የሚበሉት፡ ይሻሉና፡ አቅርቦቱ፡ ስለማይኖር፡ በህይወት፡ የመኖር፡ እጣ፡ አይኖራቸውም። ለምሳሌ፡ የውኃን፡ አቅርቦት፡ ብንወስድ፡ አሁን፡ ባለው፡ የምእራባውያን፡ የውኃ፡ ፍጆታ፡ አኪያሄድ፡(ይህም፡ ማለት፡ የአፍሪቃ፡ ሰዎች፡ ኑሯቸውን፡ ሳያሻሽሉና፡ ውኃን፡ ሳይጠቀሙ) ከሃያ፡ አመት፡ በኋላ፡ ውኃው፡ እንዲበቃ፡ ሁለት፡ አማራጭ፡ ይኖራል። አንዱ፡ አማራጭ፡ ውኃው፡ እንዲበቃ፡ ምእራባውያን፡ እንደ፡ ኢትዮጵያውያን፡ መኖር፡ አለባቸው። ምእራባውያን፡ እንደ፡ ኢትዮጵያውያን፡ መኖር፡ ባይፈልጉስ? ውጤቱ፡ ምን፡ እንደሚሆን፡ ለመገመት፡ አንባቢው፡ እርዳታ፡ የሚፈልግ፡ አይመስለኝም። ይህ፡ በውኃ፡ አጠቃቀም፡ ዘርፍ፡ ብቻ፡ ነው። በኃይል፡ ምንጭ" አጠቃእም፡ ደግሞ፡ ከዚህ፡ የባሰ፡ አደጋ፡ አለ።

መሬት፡ ከጥቅም፡ ውጭ፡ ሳትሆን፡ ልታቀርበው፡ የምትችለው፡ የኃይል፡ መጠን፡ የተወሰነ፤ ነው። ዓለም፡ በሙሉ፡ ደግሞ፡ ብልጽግናን፡ ይፈልጋል። ሁሉም፡ ከምእራባውያን፡ እንደተማረው፡ የመሬት፤ የኃይል፡ ምንጮች፡ የዘመኑ፡ የብልጽግና፡ መሠረቶች፡ ናቸው። ከጥቂት፡ አመታት፡ በኋላ፡ የዓለም፡ የኃይል፤ ምንጭ፡ ፍጆታ፡ መሬት፡ ልታቀርበው፡ ከምትችለው፡ አቅም፡ በላይ፡ ይሆናል። አፍሪቃውያን፡ በመጠኑ፡ ኑሩ፡ ቢባሉ፡ ሊኖሩ፡ ይችላሉ። ምእራባውያን፡ በመጠኑ፡ የመኖር፡ ልምድ፡ የላቸውምና፡ በመጠኑ፡ ለመኖር፡ ፈቃደኞች፡ መሆናቸውን፡ እኔ፡ አላውቅም። በመጠኑ፡ ለመኖር፡ ፈቃደኞች፡ ካልሆኑ፡ ግን፡ ከጥቂት፡ አመታት፡ በኋላ፡ አንዳንድ፡ አገሮች፡ ሌሎችን፡ ለማስወገድ፡ ሲነሳሱ፡ ልናይ፤ እንችላለን።
የውጭ፡ አገር፡ ሰዎች፡ "ልንጋራው፡ የምንችለው፡ የኃይል፡ ምንጭ፡ በጣም፡ አንሷልና፡ ካሁን፡ በኋላ፡ መኪና፡ መንዳቱ፡ ይቅርብንና፡ በሰረገላ፡ እንጠቀም፡" አይሉም። "ለምን፡ የሚጋሩንን፡ አናስወግድም፡" ማለታቸው፡ ግን አይቀርም። 

ወደፊት፡ የቅርብ፡ አደጋ፡ እንዳለብን፡ ማወቅ፡ ያሻል። ኢትዮጵያውያን፡ ይህን፡ አደጋ፡ ለመቋቋም፡ አንድ፡ ኃይልና መከታ፡ አለን። ይህ፡ ኃይል፡ ጠመንጃ፡ ወይም፡ ፓርቲ፡ ወይም፡ ሰላማዊ፡ ሰልፍ፡ ወይም፡ ደግሞ፡ ዲሞክራሲ፡ አይደለም። የኛ፡ መከታ፡ ድሮ፡ የምናውቀው፣ የሚንቁንን፡ ያዋረደ፣ ጥቂቱን፡ ያበረከተ፣ ክብርና፡ ሞገስን፡ ሰጥቶን፡ የነበረ፤ አሁን፤ ግን፤ እሱን፡ ትተን፡ እረስተነው፡ አንድ፡ ማህበር፡ እንኳን፡ ማጽናት፡ ያቃተን፡ እሱ፡ እግዚአብሔር፡ ነው። 

ኢትዮጵያውያን፡ የምንሻው፡ እግዚአብሔር፡ ያዘጋጀልንን፡ ነው፡ ካልን፡ እግዚአብሔር፡ ለኢትዮጵያ፡ ያዘዘው፡ እነሆ፡ የሚከተለውን፡ ነው፥

፩- ኢትዮጵያ፡ በንጉሥ፡ ትመራለች።
፪- ንጉሡም፡ ካዳዊት፡ ዘር፡ ይሆናል።
፫- ሥርወ፡ መንግሥቱም፡ የዳዊት፡ ሥርወ፡ መንግሥት፡ እንጂ፡ የሰሎሞን፡ ሥርወ፡ መንግሥት፡ ተብሎ፡ አይጠራም።
፬- ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር፡ አገር፡ እንጂ፡ የጋራ፡ ተብላ፡ አትጠራም።
፭- የኢትዮጵያ፡ ዋና፡ ከተማ፡ ኃይማኖቷን፡ በቅንዓት፡ ጠብቃ፡ የቆየችው፡ አክሱም፡ ትሆናለች። 
፮- ለሥራ፡ ቅልጥፍናና፤ አሠራር፡ እንዲያመች፡ ሌሎች፡ ዋና፡ ከተሞች፡ ሊኖሩ፡ ይችላሉ። ነገር፡ ግን፡ በስያሜ፡ ከአክሱም፡ የሚስተካከል፡ ወይም፡ የሚበልጥ፡ ሌላ፡ የኢትዮጵያ፡ ዋና፡ ከተማ፡ ሊኖር፡ አይችልም።
፯- ማንኛውም፡ የኢትዮጵያ፡ ንጉሥ፡ የቅብዓ፡ መንግሥት፡ ሥርአት፡ በአክሱም፡ ካልተደረገለት፡ ንጉሥ፡ ተብሎ፡ መጠራት፡  አይችልም።

የዳዊት፡ ዘር፡ የሆኑ፡ ኢትዮጵያውያን፡ በትግራይ፡ ቤት፣ በሐማሴን፡ ቤት፣ በጎንደር፡ ቤት፣ በጎዣም፡ ቤት፣ በሐድያ፡ ቤት፣ በጉራጌ፡ ቤት፣ በሸዋ፡ ቤት፣ በሐረር፡ ቤት፣ በወለጋ፡ ቤት፣ በወሎ፡ቤት፣ ወዘተ… ይገኛሉና፡ የመረጠውን፡ እግዚአብሔር፡ እራሱ፡ ይቀባዋል። በኢትዮጵያ፡ ላይ፡ በደል፡ ያልፈጸመ፡ ኢትዮጵያዊ፡ አይገኝምና፡ አሁን፡ በስልጣን፡ ላይ፡ የሚገኘውን፡ መንግሥት፡ በመቃወም፡ እሱን፡ ለመጣል፡ ጊዜን፡ በአመጽ፡ ማሳለፍ፡ አስፈላጊ፡ አይደለም። አሁን፡ በስልጣን፡ ላይ፡ የሚገኙ፡ ኢትዮጵያውያን፡ እንደሌላው፡ ኢትዮጵያዊ፡ የባእድ፡ ፍልስፍና፡ በአእምሯቸው፡ ሰርጾ፡ በመግባት፡ እነሱንም፤ እንደሌላው፡ እንቋቸውን፡ በመዳብ፡ እንዲቀይሩ፡ አስገድዷቸዋልና፡ እነሱም፡ በሽታውን፡ ሲያውቁ፡ የእግዚአብሔርን፤ ለእግዚአብሔር፡ ማስረከባቸው፡ አይቀርም።  

የኢትዮጵያ፡ ሥራ፡ ከዚህ፡ ይጀምራል። ኢትዮጵያውያን፡ እግዚአብሔር፡ እንዳዘዘው፡ ቢጀምሩ፡ እግዚአብሔር፡ ፊቱን፡ ወደ፡ ኢትዮጵያ፡ አዙሯል። የተከፈሉት፡ ይገናኛሉ፣ የተነጠቀው፡ ይመለሳል፣ ኢትዮጵያም፡ የተከበረችና፡ በረከቷ፡ የበዛ፡ ይሆናል። ኢትዮጵያን፡ በቀጥታም፡ ሆነ፡ በተዘዋዋሪ፡ ሊደፍር፡ የሚችል፡ ኃይል፡ አይኖርም። በኢትዮጵያ፡ ላይ፡ እጁን፡ ያነሳ፡ ከድንበሯ፡ ስር፡ ይንበረከካል። ኢትዮጵያን፡ ረሃብ፡ አይጎበኛትም። አበዳሪ፡ እንጂ፡ ተበዳሪ፡ አትሆንም። ልጆቿም፡ ይከብራሉ፡ እንጂ፡ በስደት፡ አይዋረዱም።

ከዚህ፡ በላይ፡ የተጻፈው፡ የፖለቲካ፡ መልእክት፡ አይደለም። ፖለቲካ፡ የሚባል፡ ቃል፡ ለስንዱ፡ ጉዳዮች፡ ተስማሚም፡ አይደለም። በምእራባዊ፡ ፍልስፍና፡ የተነደፉ፡ ሰዎች፡ በምእራቡ፡ ፍልስፍና፡ ኮልኳይነት፡ እንዲሳለቁበት፡ ለመጋበዝም፡ አይደለም። በዚህ፡ የሚሳለቁ፡ ቢኖሩ፡ ነገ፡ ሊያለቅሱ፡ ይችላሉና፡ በጥንቃቄ፡ ያስቡ። 

ይህ፡ ተከታታይ፡ መልእክት፡ ነው። የሚከታተሉት፡ መልእክቶች፡ በዚህ፡ መልእክት፡ የሚገኙትን፡ ፍሬ፡ ሃሳቦች፡ በተለያየ፡ መንገድ፡ የሚያብራሩ፡ ይሆናሉ።

   
 እግዚአብሔር፡ ይመስገን።

የስንዱ፡ ጉዳዮች።
ነሐሴ፡ ፴ ቀን፡ ፪፲፻፪፡ ዓ.ም.

በሰንጠረዡ፡ እንደምናየው፡ ምናልባትም፡ በፈረንጆች፡ አቆጣጠር፡ ከ፪፲፻፳ ዓ.ም. በፊት፡ የፍጆታ፡ መጠን፡ ከመሬት፡ አቅም፡ ሲበልጥ፡ እናያለን። የሚፈለገው፡ የኃይል፡ መጠን፡ ከመሬት፡ አቅም፡ በላይ፡ ከሆነ፡ የኃይል፡ ምንጭ፡ ከየት፡ ይመጣል? ፍላጎት፡ የግድ፡ መቀነስ፡ ሊኖርበት፡ ነው።  ፍላጎት፡ ሊቀነስ፡ የሚችለው፡ እንዴት፡ ነው? የሚለው፡ ጥያቄ፡ እያንዳንዱን፡ ኢትዮጵያዊ፡ ሊያሳስበው፡ ይገባል።
 HOME