HOME
ለኢትዮጵያ እና ከወንዞቿ ማዶ ላለች በባህር ለተከበበች አገር፥
ፈጣን መልእክተኞች መጡ። ተዘጋጁ።


በውኃ በተከበበች ከተማ በፎቅ ውስጥ ብዙ ትምህርትም ባለበት ቦታ ሆኜ ራሴን አየሁ።  ትምህርትም በመማር ላይ ነበርኹ። በፎቁ ውስጥ ካሉት ቀደም ሲል ባዕድ የነበሩ ከሚመስሉኝ ሰዎች ጋር ተቀምጨ አየሁ። እነሱም በመግባባት ያነጋግሩኝ ጀመር። በአንደበታቸውና በተግባቢነታቸው ተማረክኹ።  እንደድሮው አይደሉም፥ እንዴት ተግባቢና የሚመቹ ሰዎች ናቸው እያልኩ ሰለ ጥሩነታቸው አስቤ ሳልጨርስ በድንገት ከአስተማሪዎች አንዱ በፎቁ ላይ ወዳለችው፣ በቀዳዳዋም ባህሩን ወደምታሳየው ትንሽ መስኮት አመለከተ። በትንሿ መስኮት ውስጥ አሻግሬ ባህሩን ሳይ ከፎቁ ደቡብ አቅጣጫ ፈጣን የጀልባ መልእክተኞች  ወደዚች እኔ ወዳለሁባት በባህር ወደተከበበች ከተማ ሲቀዝፉ አየሁ። እጅግ በጣም ደነገጥኹ። ከፎቁም ሮጨ ወጣሁ። እጅግ በጣም ከመደንገጤ የተነሳ ከፎቁ ክፍል ውስጥ የነበሩት ሰዎች ወደ የት እንደሄዱ አላየሁም።

ከጀልባ ቀዛፊዎቹ ለማምለጥ ከፎቁ ወጥቸ ከፎቁ በስተሰሜን በኩል ወዳለው ባህር ገሰገስኹ። ከባህሩ መካከል የቆሙ ጀልባዎችን አየሁ። ከባህሩ ውስጥ ገብቸ እየዋኘሁ ለማምለጥ አሰብኹ።  ከባህሩ አፋፍ ስደርስ ባህሩ ለማምለጥ መልካም እንዳልሆነ አሰብኩ። ተመልሼ በፎቁና በባህሩ መካከል ባለው መንገድ ላይ ቆሜ በአይኔ ስፈልግ በስተምዕራብ በኩል ከተማውን አየሁ። ከተማውም ለማምለጥ መልካም እንዳልሆነ አየሁ። ከሩቅ በምስራቅ በኩል ያለ ተራራ አየሁ። በተራራው በኩል አመልጣለሁ ብየ አሰብኹ። ወደ ተራራውም ሮጥኹ። ከተራራውም ደረስኹ። በተራራው ላይ የእግር መንገድ አለ። ከፊት ለፊቴ የሚያነክስ ሰው መንገዴን ዘጋው። የሚያነክሰውን ሰው አለፍኩትና ከፊቱ ሆኜ መንገዴን ቀጠልኩ።  


ወገኖቼ ሆይ፥  እንደ ቀደሙ አባቶቻችን በመንቀጥቀጥና በለቅሶ ወደ እግዚአብሔር እጃችን እንዘርጋ። ከዚህ በታች ያለው የነቢዩ ኢሳይያስ መልእክት በቅርቡ፥ እጅግ በጣም በቅርቡ ይፈጸማልና።


በኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላቸው መርከቦች ላሉባት ምድር ወዮላት፥

መልእክተኞችን በባሕር ላይ ደብዳቤዎችንም በውኃ ላይ ይልካልፈጣኖች መልእክተኞች  ወደ ረዢምና ወደ ባዕድ፥ ወደ ክፉም ሕዝብ ይሄዳሉና፤ ተስፋ የቆረጡና የተረገጡ ህዝብ እነማን ናቸው? ዛሬ ግን የምድር ወንዞች ሁሉ፥ ሰዎች እንደሚኖሩባት ሃገር ይኖራሉ። በየሃገራቸው ይቀመጣሉ። ከተራሮች ራሶችም እንደ ዓላማ ይይዙታል፤ እንደ መለከት ድምፅም ይሰማል።

 እግዚአብሔር፥ "እንደ ቀትር ብርሃን ፥ በአጨዳም ወራት እንደጠል ዳመና በማደሪያየ ጸጥታም ይሆናል" ብሎኛልና።
እርሱ ከመከር በፊት አበባ በረገፈ ጊዜ የወይንም ፍሬ ጨርቋ ሲይዝ የወይኑን ቀጫጭን ዘንግ በማጭድ ይቆርጣል።  ጫፎቹንም ይመለምላል ያስወግድማል። ለሰማይ ወፎችና ለምድር አውሬዎችም በአንድነት ይቀራሉ፤ የሰማይ ወፎችና የምድር አውሬዎችም ሁሉ ይሰበስቧቸዋል። በዚያ ዘመን ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፥ ከተዋረደና ከደከመ ህዝብ፥ ከዛሬ እስከ ዘለዓለም ታላቅ ከሆነ ወገን፥ ተስፋ ከሚያደርግና ከሚረገጥ፥ በሃገሩ ወንዝ ዳር ከሚኖር ህዝብ ዘንድ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ስም በተጠራበት በደብረ ጽዮን እጅ መንሻ ይቀርባል።


ምስጋና ለእግዚአብሔር።
ህዳር ፳፯ ቀን ፪፲፻፭ ዓ.ም.