ነዳጅና የነዳጅ ነገሮች በተለይ በኢትዮጵያ ላይ ያስከተሉት ጥፋት ቁጥር ስፍር የለውም።

ከነዳጅ ጉዳቶች አንዱ ነዳጅ የመኪና ምግብ ሆኖ ያደረሰው ጥፋት ነው። መኪና የሚባለው ተሽከርካሪ ኢትዮጵያ ከገባ ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ መሠረታዊ ውድቀቶችን አስከትሏል። ከውድቀቶቹ ውስጥ ትልቁ ከመኪና የሚወጣው የተቃጠለ ጢስ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያንን የአእምሮ ዘገምተኛ ማድረጉ ነው። 

በአሜሪካ ያለ ነዳጅ እና በኢትዮጵያ ያለ ነዳጅ አንድ አይደለም። ሌድ የሚባለው ኬሚካል ያለበት ነዳጅ በአሜሪካን ሃገር በህግ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ የታገደ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ እያንዳንዱ መኪናም ሆነ ነዳጅ የሚወስድ ማናቸውም ሞተር የሚጠቀመው ሌድ ወይም በአማርኛ ቴሞን ያለበት ነዳጅ ነው። ከእያንዳንዱ መኪና የሚወጣው ጭስ ይህንኑ ሌድ የሚባል ንጥረ ነገር ይተፋል። ይህን ከመኪና የሚወጣ ጪስ በመኪና መንገድ ሲያልፍ ወይም በከተማ ሲዘዋወር ያልማገ ኢትዮጵያዊ አይገኝም። ሌድ የማገ ሰው የሚደርሱበት ብዙ አስደንጋጭ ጉዳቶች አሉበት። ከንዚህም ውስጥ አንዳንዶቹ የሚከተሉት ከ፩ እስከ ፰ የቀረቡት ናቸው።

፩- የአእምሮ ዘገምተኝነት
  
ሳይንስ በሚባለው የምዕራባውያን ኃይማኖት ጠበብት ነን የሚሉ የውጭ አገር ስዎች አጠናን እንደሚሉት ከሆነ አሥር ማይክሮግራም ሌድ በሰውነት ውስጥ ቢገኝ እነዚሁ የውጭ አገር ሰዎች የአእምሮ አገናዛቢነት በሚሉት መለኪያ ከአራት እስከ ሰባት የአእምሮ አገናዛቢነት ነጥቦችን ያጎድላል።  ለአንባቢ በሚገባ አቀራረብ ይህ ሁኔታ ምሳሌው ይህ ነው። ሁለት መንትያዎች ቢኖሩ እና አንደኛው ሌድ ባይኖርበት ሌላኛው ደግሞ አሥር ማይክሮግራም ሌድ በሰውነቱ ውስጥ ቢኖር እና ሁለቱም ጎልማሳዎች ሆነው ወፍጮ ቤት ፊት ለፊት ለጥቂት ወራት ቢኖሩ፣ ሌድ የሌለበት ጎልማሳ አንዳንድ ኩንታል የተፈጨ እህል በማጅራታቸው እየተሸከሙ የሚሄዱ ሠራተኞችን አይቶ ድካማቸው አስጨንቆት ሥራቸውን ለማቅለል የሚጎተት ጋሪን ይሰራና በሽያጭ ወይም በብድር እንዲጠቀሙበት ያቀርብላቸዋል። አሥር ማይክሮግራም ሌድ በሰውነቱ ውስጥ ያለበት ጎልማሳው ወንድሙ ግን ሠራተኞቹ  አድካሚ ሥራ እንደሚሰሩ እንኳን ማስተዋል አይችልም እንደማለት ነው። መኪና ከገባ ጊዜ ጀምሮ ለኢትዮጵያዉያን የተቀላጠፈ ውድቀት አንዱን አስተዋጽኦ ያደረገው ይሄው በተቃጠለ የነዳጅ ጢስ ወደኢትዮጵያውያን ሰውነት የገባው ሌድ ነው። አሥር ማይክሮ ግራም በአይን እንኳን ለማየት የሚያዳግት መጠኑ ትንሽ ነው። በኢትዮጵያ በእያንዳንዱ መኪና በየሰአቱ የሚረጨው ሌድ ብዙ ሰዎችን በአንድ ጊዜ የሚመርዝ ብዙ መጠን አለው። ጉዳቱም ከላይ ከተጠቀሰው እጅግ የከፋ ነው። በተለይም በከተሞች እና በአዲስ አበባ ብዙ ሰዎች ከቁምነገረኝነት ይልቅ ቅጥፈትና ሌብነት፣ ከትጋት ይልቅ ማጭበርበር፣ ከሥራ ይልቅ ወሬ ወዳዶች የሆኑበት አንዱ ከቆዳ ሥር የተደበቀ መንስኤ ይሄው ነው። 

፪- የአእምሮ ጭጋግና የራስ ምታት

ከመኪና የጢስ ማዉጫ የሚወጣው ሌድ ለብዙ ሰዎች የህሊና መደቆስን እና የራስ ህመም በሽታን ይሰጣል። ብዙ የኢትዮጵያ ከተማ ሰዎች በቀን ውስጥ አብዛኛውን ሰዓት ከመንፈስ መነቃቃት ይልቅ እንደጭጋግ የሚያዳፍን የተደቆሰ ስሜት ይኖራቸዋል።

፫- የማስተዋል ግድፈት

በሌድ የተበከሉ ሰዎች የሚያዩትን ነገር መርምረው ምን እንደሆነ ለይተው የማወቅ መነቃቃት የላቸውም። የአካባቢያቸውን ውድቀት በውን የመለየት ማስተዋል የላቸውም። ውድቀቱ ቢነገራቸውም የመነቃቂያ ነርቫቸው በሌድ ስለተኮላሸ አካባቢያቸውን ለማሻሻል የመሻት መነቃቃት የላቸውም።

፬- የእጅ እንቅስቃሴ ጎልዳማነት

ሌድ ቀልጣፋና አስተካክሎ የሚሠራ እጅን ይነሳል። በሌድ የተበከሉ ሰዎች የእጅ እንቅስቃሴያቸው ወደሽባነት የተጠጋ ሊሆን ይችላል። ሌድ ከሰው ሰው የሚያደርሰው ጉዳት ሊለያይ ይችላልና ሁሉም በሌድ የተበከሉ ሰዎች የእጃቸው እንቅስቃሴ እንደሽባ ይሆናል ብሎ መጠበቅ አያስፈልግም። 

፭- ቁጡነትና ተስፋ ቆራጭነት

በሌድ መመረዝ ቁጡነትን ሊያስከትል ይችላል። ከመኪና መምጣት ወዲህ ኢትዮጵያውያን በፍቅርም ሆነ በሥራ ማህበር ተስማምተው የማይቆዩበት በሽታ አንዱ የተደበቀ መንስኤው ይሄው በሌድ መበከል ነው።  

፮- ድካምና የስንፍና ስሜት

ሌድ በሰውነቱ ውስጥ የሚገኝ ሰው ብዙ ጊዜ የድካም ስሜት ይሰማዋል። ለሥራ ከመነቃቃት ይልቅ ለማንቀላፋት ወይም በወንበር ዙሪያ ቁጭ ብሎ ወግ ማውጋትን ብቻ ይሻል። ከስንፍና ስሜት የተነሳም ሥራን ይሸሻል። ሥራን ላለመስራትም ብዙ ምክንያቶችን ያቀርባል። እነዚህ ሥራን ላለመሥራት የቀረቡ ምክንያቶች ሌሎችም ሰዎች ሥራ እንዳይሰሩ የሚያሰናክሉ እስከመሆን ሊደርሱ ይችላሉ።

፯- የሰውነት አቋም መዛባት

ሌድ የሰውነትን ቅርጽና የአቋቋም ሚዛንን ያዛባል። በተለይ ከክንድ በታች እጅ ይዝላል።፡ እጅ የእጅ ማጠፊያ ሽባነትን የሚመስል አወዳደቅ ሊታይበት ይችላል። የሌድ መርዝ ያለበት ሰውነት በተፈጥሮ የታደለው አደጋን የመከላከል ቅጽበታዊ የመመከት ችሎታው ይወሰድበታል።

፰- የኩላሊት በሺታ

ሌድ በሰውነቱ ውስጥ የገባ ሰው የኩላሊት ማጣሪያው በሌድ ሊበከል ይችላል። የኩላሊት በሽታ ደግሞ የሚጎዱ ሌሎች የሰውነት ድክመቶችን ያስከትላሉ።

በደልን አለማወቅ

ነዳጅ ብቻ ሳይሆን የኢንዱስትሪ ውጤት የሆኑ የትኞቹም ሸቀጦች በተለያየ መንገድ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ላይ ውድቀትን አስከትለዋል። ይህ ማለት ግን ሁሉንም የኢንዱስትሪ ውጤቶች ወዲያውኑ ማስወገድ ያስፈልጋል ማለት አይደለም። ቁስል በአንድ ጊዜ አይድንም። ኢትዮጵያም ወንዝ አፈራሽ ወደሆነው ፈሪሃ እግዚአብሔር ወዳለው ስልጣኔዋ በአንድ ምሽት አትመለስም። ከሌሎች የተዋሰቻቸውን ምርቶች ጥቅም እና ጉዳታቸውን እንደቤቷ መርምራ የሚጠቅሙትን መያዝ የሚጎዱትን ማስወገድ ይጠቅማታል።

ለምሳሌ ለቁጥር የሚያስቸግር የቤት መኪና ወደ አገር ውስጥ ማዥጎድጎድ ከጉዳት በቀር ጥቅም ያለው ነገር አይደለም። የቤት መኪና አንዱ ኢትዮጵያዊ በሌላው ኢትዮጵያዊ ላይ የቁሳቁስ የበላይነትን ስሜት ፈጥሮ መኪና ለመግዛት የሙስናና የማምታታት ውድድርን ከማበረታታት ውጭ የሚሰጠው ጥቅም የለም። በኢትዮጵያ ውስጥ ከድንበር እስከድንበር የሚደርስ ባቡር፣ ምቾት ያላቸው አውቶቡሶች እና የእቃ ማመላለሻ ትሽከርካሪዎች ይበቃሉ። መኪና ከውጭ አገር ከመግዛት በየሰፈሩ ሠረገላ መሥራት የበለጠ ጥቅም አለው። የባቡር ሃዲድ ሰርቶ በባቡር መገልገል ደግሞ የተሻለ ነው ምክንያቱም በአንድ የባቡር ጉዞ ብዙ ሺህ መኪናዎች የሚሸከሙትን ማጓጓዝ ይቻላል። ባቡር የሚያደርሰው ጥፋት አንድ መኪና ከሚያደርሰው ጥፋት አይበልጥም። አንድ የቤት መኪና ግን አንድ ሰው ለማቀናጣት በመቶ ወይም በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን የአዕምሮ ዘገምተኛ እና በሽተኛ እንዲሁም ድሀ ያደርጋል። ይህ አንድ መኪና ሰውን ካማቀናናትና ለሌብነት ከማበረታታት አልፎ ይህ ነው የሚባል ጥቅም እምብዛም የለውም። እያንዳንዱን መኪና በመርዘኛው ነዳጅ ለማንቀሳቀስ ደግሞ እጅግ የበዙ የሃገር መልካም ምርቶችን ለውጭ ሃገር ሰዎች ሰጥቶ በምትኩ የውጭ ዶላር ገብይቶ ለዚሁ ለነዳጅ ማፍሰስን ይጠይቃል። የመኪና ጉዳቱ በብዙ አቅጣጫ ነው። 

አምላክ ሆይ ስምህ ይቀደስ።

መኪና ጭስ እየተፋች ፈጠነች፤
ስንዱ ጭሱን ምጋ ዘገመች።


 HOME
ቴሞን (የሌድ መርዝ) ያስከተለው ጉዳትና የወደፊቷ ኢትዮጵያ።